ውይይቱም በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ሃላፊ በአቶ መሐመድ ያህያ ሰብሳቢነት የገቢዎች ቢሮ፤ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ፤ የሐረር ማዘጋጃ ቤት እና የፕላንና ልማት ኮሚሽን በተገኙበት በቀረበው የ2017 በጀት አመት የገቢ ዕቅድ ላይ በስፋት እና በጥልቀት ተወያይተዋል ።
በክልል ደረጃ ታቅደው እየተከናወኑ የሚገኙትንና የቅድሚያ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ለሚሰሩ የልማት ስራዎች ትልቁን ድርሻ የሚይዘው ከክልሉ ውስጥ የሚሰበሰብ ገቢ መሆኑን ተገልጿል ።
በዚሁ መሰረት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የገቢ ዕቅዱ ላይ በስፋት በመወያየት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ የ2017 በጀት ዓመት ከክልሉ የሚሰበሰብ ገቢ እቅድን በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል ።
በመጨረሻም የኮሚቴው ሰብሳቢ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ ያህያ ባስተላለፉት መልዕክት ባለድርሻ አካላት ይህን የገቢ ዕቅድ ላይ ከውሳኔ በመድረሳቸውና እንዲሁም በቅንጅት ለመስራት ላሳዩት ቁርጠኝነት በቢሮው እና በኮሚቴው ስም በማመስገን ውይይቱ ተጠናቋል ።