ከዓለም ባንክ በተገኘ የፋይናንስ ድጋፍ የሚካሄደው የማህበራዊ ተጠያቂነት ፕሮግራም የማህበራዊ ተጠያቂነትን በማስፈን ዜጎች ጥራት ያለው መሠረታዊ አገልግሎቶች እንዲያገኙ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ተገልጿል ፡፡
ፕሮግራሙን ከሚያሰፈፅመው አሚር ኑር ወረዳ መስተዳድር አስተዳዳሪዎች፣ አፈ ጉባዔዎችና በወረዳው ተጋላጭ አካላት ጋር የውይይት መድረክ ሲካሄድ በገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የማህበራዊ ተጠያቂነት አስተባባሪ አቶ አዲብ መሐመድ እንደተናገሩት የፕሮግራሙ ዋነኛ ዓላማ የማህበራዊ ተጠያቂነት ሥርዓት እንዲጠናከር ድጋፍ በማድረግ ዜጎች ጥራት ያለው መሠረታዊ አገልግሎቶች እንዲያገኙ ማስቻል ነው ብለዋል፡፡
መንግስት በትምህርት፣በግብርና፣ በጤና፣ በውሃና በመንገድ መሰረተ ልማቶች የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል የተለያዩ ተግባራት በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አቶ አዲብ ጠቅሰው መንግስት በሚያከናውነው መሰረታዊ አገልግሎቶች ላይ ማህበረሰቡ ውሰጥ የባለቤትነት ስሜት እንዲፍጠር በማስቻል ህዝቡ የበኩልን የድርሻ እንዲወጣ ፕሮግራሙ እድል የፈጠረ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የማህበራዊ ተጠያቂነት ፕሮግራም ባለፈው አመት ተተግብሮ ጥሩ ውጤት የተገኘ ሲሆን በዚህ አመት በአሚር ኑር ወረዳ ተግባራዊ ለማድረግ ስራዎች ተጀምሯል